Benishangul Gumuz Regional Education Bureau Grade 6th 8th Exam 2018: Sixth and eighth grade exam preparation is being done according to the scheduled schedule. n
Benishangul-Gumuz Regional Education Office stated that the sixth and eighth grade exam preparation is being conducted according to the scheduled schedule.
Grade 8th & Grade 6th Exam Preparation 2018/2026
Mr. Mohammed Usman, the vice head of the office of system education & educational institutions, has visited the examination and evaluation department and observed the preparation of the sixth grade regional exam.
In their opinion, they mentioned that the exam is being organized according to the scheduled schedule. They said that this year the exam is given to candidates and the exam will be fixed by machine and the result will be announced to the students quickly.
The office is already working to complete software and similar works and preparation for 6th and 8th grade exams is already underway; the office is closely monitoring and supporting regional and national exams; from the preparation to the end of the exams, the office is working to complete the exams successfully, Mr. Mohammed Aklew mentioned.
The exam assessor of the office Mrs. Meziwet Gizaw has told us that the preparation for the 8th grade exam at Gilgel Beles Teachers Training College is over.
It is said that 25,045 6th grade students and 21,534 8th grade students will take the exam this year. The report is from the communication directorate of the office.
Benishangul Gumuz Regional Education Bureau Grade 6th 8th Exam 2018
የስድስተኛና የስምንተኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት በተያዘለት መርሀ-ግብር እየተከናወነ ነው
(ግንቦት 11/2018 ዓ.ም ፤ አሶሳ) የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ የስድስተኛና የስምንተኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት በተያዘለት መርሀ-ግብር እየተከናወነ ሲል ገለጸ፡፡
በቢሮው የስርዓተ-ትምህርትና የትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ኡስማን በፈተናና ምዘና ክፍል ተገኝተው የስድስተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዝግጅትን ተመልከተዋል፡፡
በምልከታቸውም ፈተናው በተያዘለት መርሀ-ግብር እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው ፤ በዚህ ዓመት ፈተናው ለተማሪዎች ተሰጥቶ እንደተጠናቀቀ ፈተናው በማሽን ታርሞ በፍጥነት ውጤት ለተማሪዎች ይገለጻል ብለዋል፡፡
የሶፍትዌርና መሰል ስራዎችን ቢሮው ከወዲሁ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ሲሆን የ6ኛና የ8ኛ ክፍል ፈተና ዝግጅት ከወዲሁ እየተከናወነ ይገኛል ፤ ቢሮውም በቅርበት ክልል አቀፍና ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን በቅርበት ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ፤ ከፈተና ቅድመ ዝግጅት እስከ ፍጻሜ ድረስ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ቢሮ እየሰራ ነው ሲሉ አቶ መሀመድ አክለው ጠቅሰዋል፡፡
የስምንተኛ ክፍል ፈተና በግልገል በለስ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዝግጅቱ ተጠናቋል ሲሉ በቢሮው የፈተና ምዘና ባለሙያ ወ/ሮ መስታወት ግዛው ገልጸውልናል፡፡
በዚህም ዓመትም 25,045 የ6ኛ ክፍል እንዲሁም 21,534 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል፡፡ ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው

